Home Entertainment News ጆርጅ ፍሎይድን የገደለው የቀድሞው ፖሊስ መኮንን ዴሪክ ቻውቪን ከ 22 ዓመት በላይ እስር ተፈረደበት

ጆርጅ ፍሎይድን የገደለው የቀድሞው ፖሊስ መኮንን ዴሪክ ቻውቪን ከ 22 ዓመት በላይ እስር ተፈረደበት

by sam

ባለፈው ዓመት ግንቦት ሚኒሶታ ውስጥ አፍሪካ አሜሪካዊውን ጆርጅ ፍሎይድን በመግደል ወንጀል የተከሰሰው አሜሪካዊው ነጭ የቀድሞ የፖሊስ መኮንን 22 ዓመት ከስድስት ወር እስር ተፈረደበት።

የዴሪክ ቻውቪን ቅጣት “የተጣለበትን እምነት እና ኃላፊነት በማጉደል እንዲሁም በታየው ልዩ ጭካኔ” ላይ የተመሠረተ መሆኑን ዳኛው ተናግረዋል።

የ48 ዓመቱ ጆርጅ ፍሎይድ ህይወት ያለፈው ቻውቪን አንገቱ ላይ ለዘጠኝ ደቂቃዎች የህል ተንበርክኮ ተንፋሽ አሳጥቶት ከቆየ በኋላ ነበር።

ግድያው ዘረኝነትን እና የፖሊስ ጭካኔን ሚቃወሙ ዓለም አቀፍ ተቃውሞዎችን አስከትሏል።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish