ይህን የሆነው የራሳቸው ኩባንያ ለ17 ዓመታት ሲያስገነባት በነበረች ሮኬት ነው። ይህች ሮኬት ቨርጂን ጋላቲክ ዩኒቲ ትባላለች።
ይህን የሳቸውን የተሳካ የጠፈር ጉዞን ተከትሎ ወደ ሕዋ መዝለቅ ተራ የቱሪዝም ጉዳይ ሊሆን ተቃርቧል።
ከአሜሪካ ኒው ሜክሲኮ ግዛት ተነስታ ሽቅብ የተምዘገዘገችው ቨርጂን ጋላቲካ ሮኬት 17 ዓመታት የተደከመባት ናት።
ቢሊየነሩ ሰር ሪቻርድ የጠፈርን ጫፍ ተጠግተው ወደ ምድር ከተመሰሉ በኋላ ይህ “በሕይወቴ ልዩ ተአምር ነው” ብለዋል።
ቢሊየነሩ ወደ ምድር የተመለሱት ምድርን ከለቀቁ ከአንድ ሰዓት በኋላ ነው።