Home Entertainment News ደቡብ ኮሪያ በስፖርት ማዘውተሪያዎች ውስጥ ፈጠን ያሉ ሙዚቃዎች መጫወትን አገደች

ደቡብ ኮሪያ በስፖርት ማዘውተሪያዎች ውስጥ ፈጠን ያሉ ሙዚቃዎች መጫወትን አገደች

by sam

በደቡብ ኮሪያ የሰውነት ማጎልመሻ ማዕከላት ወይም በጂም ውስጥ የሚከፈቱ ሙዚቃዎች ለስለስ ያሉ እንዲሆኑ ደንብ ተላለፈ፡፡

ይህም የሆነው ፈጣን ምት ያላቸው ሙዚቃዎች ላብ እንዲፈጠር ስለሚያደርጉ፣ እንዲሁም ሰዎች ቶሎ ቶሎ እንዲተነፍሱ ምክንያት ስለሚሆኑ ነው፡፡

ይህ ሁኔታ ደግሞ በዋናነት የኮቪድ ሥርጭትን ሊያስፋፋ ስለሚችል ለስላሳ ሙዚቃዎች ማጫወት በተዘዋዋሪ ኮቪድን ሊገታ ይችላሉ ተብሎ የተዘየደ መላ ነው ተብሏል፡፡

በዚህ መመርያ መሰረት 120 ቢት በደቂቃ እና ከዚያ በታች የሆነ ምት ያላቸው ሙዚቃዎች ናቸው ተገቢ የሚሆኑትና በሰውነት ማጎልመሻዎቹ ውስጥ መጫወት የሚችሉት፡፡

ተንቀሳቃሽ ያልሆነ የመሮጫ መም (ትሬድሚል) ደግሞ ቢበዛ በሰዓት 6 ኪሎ ሜትር ብቻ እንዲፈጥን እንዲደረግ ታዟል፡፡

የጤና ባለሞያዎች እንደሚሉት ይህ መመሪያ ተግባራዊ ሲደረግ በስፖርት ማጎልመሻ ማዕከላት ውስጥ የሚገኙ ሰዎች አተነፋፈሳቸው ከልክ በላይ እንዳይሆን፣ ላባቸውም እንዳይንቆረቆር ያስችላል፡፡ይህም የኮቪድ ስርጭትን ይቀንሳል ብለዋል፡፡

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish