Home Sport News ሊዮኔል ሜሲ እና ክርስቲያኖ ሮናልዶ

ሊዮኔል ሜሲ እና ክርስቲያኖ ሮናልዶ

by sam

ሁለቱ የእግር ኳስ ኮከቦች በክረምቱ የአለም አቀፍ ውድድሮች ላይ ለ ሀገራቸው ትልቅ ድርሻን ተወጥተው አሳልፈዋል ።

ሊዮኔል ሜሲ በ ኮፓ አሜሪካው ለሀገሩ ተጨማሪ አምስት ጎሎችን እና አምስት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል ።

ሊዮኔል ሜሲ በቀጣይ ለ ሀገሩ አርጀንቲና አንድ ግብ ካስቆጠረ በ ደቡብ አሜሪካዊ ተጫዋች ብዙ ጎሎችን በማስቆጠር የ ፔሌን ሪከርድ ይጋራል ።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ ተጨማሪ ስድስት ጎሎችን እና አንድ ለ ግብ የሚሆን ኳስን ለ ሀገሩ ባለፉት ወራት ሲያስቆጥር በቀጣይ አንድ ግብ የሚያስቆጥር ከሆነ በአለም አቀፍ ውድድሮች ላይ የምንጊዜም ግብ አግቢ ሪከርድን የግሉ ያደርጋል ።

በቀጣይ በ ወርሀ መስከረም ፖርቹጋል ከ አይርላንድ እንዲሁም ቬንዙዌላ ከ አርጀንቲና በ አንድ ቀን ልዩነት ጨዋታቸውን ያካሂዳሉ ።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish