Home Entertainment News ቢሊየነር ጄፍ ቤዞስ የተሳከ የጠፈር በረራ አድርጎ ወደ ምድር ተመለሰ

ቢሊየነር ጄፍ ቤዞስ የተሳከ የጠፈር በረራ አድርጎ ወደ ምድር ተመለሰ

by sam

ቢሊየነር ጄፍ ቤዞስ የግሉ ሮኬት በሆነችው ‘ኒው ሸፈርድ’ ከመጀመሪያ የበረራ ቡድን ወደ ጠፈር የተሳካ በረራ አድርጎ ወደ ምድር ተመለሰ።

ወንድሙ ማርክ ቤዞስ ፣ የ82 ዓመቷ የጠፈር ውድድር ፈር ቀዳጅ ዋሊይ ፈንክ እና የ18 ዓመት ተማሪ አብረው ተጉዘዋል።

ጉዟቸውን ያደረጉት ትልቅ መስኮት ባላት አነስተኛ መንኮራኩር ነው። ይህም መሬትን በአስገራሚ ሁኔታ ለማየት የሚያስችል ነው ተብሏል።

‘ኒው ሸፈርድ’ የተባለችው መንኮራኩር የተሰራችው በቤዞስ ድርጅት ‘ብሉ ኦሪጅን’ ሲሆን የተሠራችው ገበያው እየደራ ለመጣው የጠፈር ጉብኝት ነው።

መንገደኞቹ ለጠፈር ሳይንስ እንግዳ ያልሆኑትን አዛውንት ፋንክን እና ወጣቱን ተማሪ ኦሊቨር ዴሜንን ያካተተ ነው።

ቢሊየነሩ ቤዞስ ከበረራው በፊት ለሲቢኤስ በሰጠው ቃለ ምልልስ ላይ “በጣም ደስ ብሎኛል! ሰዎች ፈርቼ እንደሆነ እየጠየቁኝ ነው። እኔ ግን ጭራሽ ፍርሃት የሚባል ነገር የለኝም። ይልቁንስ በጣም ጓጉቻለሁ። ምን ልንማር እንደምንችል ማወቅ እፈልጋለሁ” ብሎ ነበር።

“ሥልጣና ወስደናል። መንኮራኩሯም ዝግጁ ናት ። መንገደኞቹም እንዲሁ። ቡድኑ በጣም አስገራሚ ነው። አሁን ላይ ጥሩ ነገር ነው የሚሰማን” ሲሉ ቤዞስ ከበረራው በፊት ተናግሯል።

ወደ ጠፈር በመጓዝ ፈር ቀዳጅ የሆኑት ፈንክ በ1960ዎቹ ሜርኩሪ 13 የተባለ የሴቶች ቡድን አባል ነበሩ። ፈንክ ከወንዶች የጠፈር ተመራማሪዎች ተማሳሳይ ፈተና የወሰዱ ቢሆንም ወደ ጠፈር ተጉዘው አያውቁም። ለበርካታ ጊዜ ወደ ጠፈር ለመጓዝ ግን ሙከራ አድርገዋል።

ዋሊይ ፈንክ ከቀደምት የናሳ እጩ ጠፈርተኞች አንዷ ነበሩ።

እነዚህ አራቱ መንገደኞች ዛሬ ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ በቴክሳስ ቫን ሆርን አቅራቢያ ከሚገኘው ከቤዞስን የግል የመንኮራኩር ማስጀመሪያ ሥፍራ በረዋል።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish