Home Entertainment News በኮሮና የተያዘው ኢንዶኔዥያዊ ባለቤቱን መስሎ በአውሮፕላን ሲጓዝ ተያዘ

በኮሮና የተያዘው ኢንዶኔዥያዊ ባለቤቱን መስሎ በአውሮፕላን ሲጓዝ ተያዘ

by sam

በኢንዶኔዥያ በሃገር ውስጥ በረራ ላይ በኮቪድ-19 የተያዘ አንድ ግለሰብ ሚስቱን ተመስሎ ሲበር መያዙ ተገልጿል።

ዲ ደብልዩ የተባለው ይህ ግለሰብ በአውሮፕላን ውስጥ ለመሳፈር ኒቃብ በመባል የሚታወቀውን ሙሉ የፊት መሸፈኛ ለብሶ ነበር ተብሏል።

ግለሰቡ የባለቤቱን ፓስፖርት እና ኔጋቲቭ የኮቪድ ውጤቷንም ይዞ ነበር።

በበረራው መካከል ወደ መደበኛው ልብሱ ባይለውጥ ኖሮ አይያዝም ነበር። ልብሱን በሚቀይርበት ወቅት የአውሮፕላኑ አስተናጋጆች ማያታቸውን ተከትሎም ነው የተያዘው።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish