Home Entertainment News ዝነኛው አሜሪካዊ ቲክቶከር ሲኒማ ቤት በተከፈተበት ተኩስ ተገደለ

ዝነኛው አሜሪካዊ ቲክቶከር ሲኒማ ቤት በተከፈተበት ተኩስ ተገደለ

by sam

አሜሪካዊው ቲክቶከር እና አንድ ጓደኛው በደቡባዊ ካሊፎርኒያ ሲኒማ ቤት በጥይት እንደተገደሉ ከፖሊስ እና ከሟች ቤተሰብ ተረጋግጧል።

በቲክቶክ በሚሠራው ቪዲዮ ዝናን ያተረፈውና አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ተከታዮች የነበሩት የ19 ዓመቱ አንቶኒ ባራጃስ እና የ18 ዓመቱ ራይሊ ጉድሪክሪች የተባለው ጓደኛው በኮሮና ግዛት በሚገኝ ሲኒማ ቤት ውስጥ ጭንቅላታቸው ላይ በተተኮሰባችው ጥይት ለህልፈት ተዳርገዋል።

ራይሊ ከጥቃቱ በኋላ ወዲያው የሞተ ሲሆን አንቶኒ ግን በሕይወት ቆይቶ የነፍስ ማዳን ክትትል ሲደረግለት ነበር። ሆኖም ከጥቂት ጊዜ በኋላ ሕይወቱ ማለፉን ቤተሰቡ አስታውቋል።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish