Home Entertainment News ሲኤንኤን ያልተከተቡ ሰራተኞቹ ቢሮ በመሄዳቸው ከስራ አባረረ

ሲኤንኤን ያልተከተቡ ሰራተኞቹ ቢሮ በመሄዳቸው ከስራ አባረረ

by sam

የአሜሪካ የዜና አውታር ሲኤንኤን የኮቪድ-19 ክትባት ሳይከተቡ ቢሮ የገቡ ሶስት ሰራተኞቹን ማሰናበቱን የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ኩባንያው አስገዳጅ የክትባቱን ህግ የጣሱ ሰራተኞቹን ሲያባርር የመጀመሪያው ኩባንያ ነው ተብሏል።

በአሜሪካ ውስጥ ያሉ ኩባንያዎች ሰራተኞቻቻውን እንዲከተቡ የመጠየቅ ህጋዊ መሰረት አላቸው።

ፌስቡክን እና ጉግልን ጨምሮ በርካታ ትልልቅ ኩባንያዎች በሚቀጥሉት ወራቶች ውስጥ ቢሮቻቸው ሙሉ በሙሉ ሲከፈቱ ሠራተኞቻቸው ተከትበው መምጣት አለባቸው ብሏል።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish