ከ4 ሺህ 500 ዕድሜ በላይ ያስቆጠረና በፈርዖኖች የተገነባ አንድ አስደናቂ ጥንታዊ የግብፅ ጀልባ በጊዛ በሚገኘው በታላቁ የግብፅ ሙዚየም እንዲዛወር ተደርጓል።
ጀልባውን የሰራው ከ 2,589-2,566 ዓመተ ዓለም እንደ ነገሠ የሚታመነው ንጉሥ ኩፉ ሲሆን በጥንቶቹ ግሪኮች ቺዮፕስ በመባል ይታወቅ ነበር
የንጉስ ኩፉ ታላቁ ጀልባ ከ 4,500 ዓመታት በላይ ዕድሜ ያለው ሲሆን በ አውሮፓውያኑ 1954 ሲገኝም ሙሉ በሙሉ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደነበረ ነው
የጣውላ ጀልባውን ወደ አዲሱ ቋሚ ማሳያ ሙዚየሙ ለማንቀሳቀስ ትልልቅ ማሸኖችን ተጠቅመዋል