Home Entertainment News በቻይና ጥንዶች እስከ 3 ልጆች እንዲወልዱ ተፈቀደ

በቻይና ጥንዶች እስከ 3 ልጆች እንዲወልዱ ተፈቀደ

by sam

ቻይና የሶስት ልጆች ፓሊሲ በተሰኘ ማዕቀፍ ባለትዳሮች እስከ ሦስት ልጆች እንዲኖራቸውው በመፍቀድ የወሊድ ምጣኔንን የተመለከተውን የቀድሞ ደንቧን አሻሽላለች።

አዲሱ ደንብ ባለፈው አርብ በሀገሪቱ ከፍተኛ የሕግ አውጭዎች በብሔራዊ ህዝባዊ ኮንግረስ ጉባኤ ላይ ከጸደቁ በርካታ ህጎች አንዱ ነው። እናም ይህንን ደንብ ዘግይቶ የተሻሻለ ሲሉ ነበር የሆንግ ኮንግ ሚዲያዎች የዘገቡት።

ቻይና መሰረታዊ የፖሊሲ ለውጥ በማድረግ ባለትዳሮች እስከ ሦስት ልጆች እንዲወልዱ እንደምትፈቅድ በዚህ ዓመት ግንቦት ወር ላይ ነበር ያሳወቀችው።

ታዲያ አርብ’ለት የግንቦቱ ውሳኔ የወሊድ ምጣኔን ከፍ ለማድረግ እና ልጅን ለማሳደግ ያለውን “ሸክሙን ለመቀነስ” በማለም መደበኛ በሆነው የህግ ስርዓት መጽደቁን ዢንዋ የዜና ወኪል ዘግቧል።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish