Home Entertainment News ዋየር ፊልም ተዋናዩ ማይክል ኬ ዊልያምስ ሞቶ ተገኘ

ዋየር ፊልም ተዋናዩ ማይክል ኬ ዊልያምስ ሞቶ ተገኘ

by sam

በኤች.ቢ.ኦ. ቴሌቪዥን ተከታታይ ፊልም የሆነው ‘ዘ ዋየር’ ዋነኛ ተዋናይ የሆነው አሜሪካዊው ተዋናይ ማይክል ኬኔት ዊልያምስ በኒውዮርክ አፓርታማው ውስጥ ሞቶ ተገኝቷል። ተዋናዩ ዕድሜው 54 ነበር።

የአሜሪካ ሚዲያዎች የአሟሟቱን ምክንያት በተመለከተ የሕግ አስከባሪ ምንጮችን ጠቅሰው እንደዘገቡት ከመጠን በላይ የአደንዛዥ ዕፅ ከመውሰድ ጋር ጥርጣሬ ቢሆንም ይህ ግን በይፋ አልተረጋገጠም።

ስመ ጥር በሆነው የኤሚ ሽልማት ሶስት ጊዜ በእጩነት የቀረበው ሚካኤል ባለፉት ዓመታት ከአደንዛዥ ዕጾች ጋር ስለነበረው ትግል በግልፅ ሲናገርም ነበር።

ከፍተኛ አድናቆትን ባተረፈው ‘ዘ ዋየር’ ተከታታይ ፊልም ኦማር ሊት የተባለ፣ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ፣ የጎዳና ላይም የዕፅ አዘዋዋሪ ዋነኛ ሰውን የወከለ ገፀ ባህርይ ተጫውቷል።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish