Home Entertainment News የልዑል ፊሊፕ ኑዛዜ ለ90 ዓመታት በምስጢር እንዲያዝ ፍርድ ቤት አዘዘ

የልዑል ፊሊፕ ኑዛዜ ለ90 ዓመታት በምስጢር እንዲያዝ ፍርድ ቤት አዘዘ

by sam

የዳግማዊት ንግሥት ኤልዛቤት ባለቤት የነበሩት የልዑል ፊሊፕ ኑዛዜ ለ90 ዓመታት በምስጢር እንዲያዝ ፍርድ ቤት አዘዘ።

የኤደንብራው መስፍን ልዑል ፊሊፕ ከህልፈታቸው በኋላ ንብረታቸውን በተመለከተ ያሰፈሩበት መዝገብ የንግሥቲቱን “ክብር እና አቋም” ለመጠበቅ ሲባል ቢያንስ ለ90 ዓመታት ምስጢር ሆኖ እንዲቆይ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወስኗል።

የንጉሣዊው ቤተሰብ ከፍተኛ አባል ከሞተ በኋላ ፍርድ ቤቶች ኑዛዜያቸው በምስጢር እንዲጠበቅ የንጉሣዊው ችሎትን ውሳኔ ይፈልጋል።

ይህም ማለት ከተለመደው ንብረታቸው ውጪ የንጉሣሳዊ ቤተሰቡ ኑዛዜ ለሕዝብ ይፍ አይሆንም ማለት ነው።

ታዲያ የልዑሉን ቃል በዘላቂነት ምስጢር አድርጎ ለማቆየት ወይም ላለማቆየት ለመወሰን በ90 ዓመታት ውስጥ የግል ሂደት ይኖራል ተብሏል። በቤተሰብ ጉዳዮች ከፍተኛ ልምድ ያላቸው ዳኛ አንድሪው ማክፋርሌን የመሩት ችሎት ላይ ኑዛዜውን በምስጢር ለማቆየት የቀረበውን ማመልከቻ ከወራት በፊት በዝግ ነበር የታየው።

ዳኛው ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግን፣ የመንግሥት የሕግ አማካሪንና ልዑሉን የሚወክሉ ጠበቆችን አከራክረው ሐሙስ ዕለት የልዑል ፊሊፕ ኑዛዜ በሚስጥር እንዲቆይ ውሳኔ አሳልፈዋል።

ዳኛው ከ30 በላይ በምስጢር የተያዙ የንጉሣዊ ቤተሰቦች ኑዛዜዎች መኖራቸውንም የጠቆሙ ሲሆን እነዚህም ከ100 ዓመታት በኋላ ይፋ ሊደረጉ የሚችሉበት እድል እንዳለ ተናግረዋል።

እናም በቅርቡ ህልፈታቸው የተሰማው የንግሥቲቱ ባለቤትና የኤደንብራው መስፍን ልዑል ፊሊፕ የኑዛዜያቸውን ቃል የያዘው ሰነድ ከ90 ዓመታት በኋላ ይፍ ይሆናል።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish