Home Entertainment News የኮሪያው ፊልም ‘ስኩዊድ ጌም’ በኔትፍሊክስ ታሪክ አንደኛ የታየ ሆኖ ተመዘገበ

የኮሪያው ፊልም ‘ስኩዊድ ጌም’ በኔትፍሊክስ ታሪክ አንደኛ የታየ ሆኖ ተመዘገበ

by sam

ስኩዊድ ጌም የተሰኘው የኮሪያ ፊልም በኔትፍሊክስ ታሪክ በርካታ ሚሊዮኖች የተመለከቱት ተከታታይ ፊልም ሆኖ ተመዝግቧል።

ደቡብ ኮሪያ ውስጥ የተሰራው የድራማ ዘውግ ያለው ትዕይንት እስካሁን ድረስ መቶ አሥራ አንድ ሚሊዮን ተመልካቾች አይተውታል።

ከዚህ በፊት በኔትፍሊክስ ከፍተኛ ተመልካች አግኝቶ የነበረው ብሪጀርተን የተሰኘው ተከታታይ ፊልም ነበር። 

ይህ ተከታታይ ፊልም በ88 ሚሊዮን ተመልካቾች ታይቷል። ኔትፍሊክስ የተሰኘው የበይነ መረብ ፊልም ማሳያ ገፀ አንድ ሰው አንድን ፊልም ለሁለት ደቂቃና ከዚያ በላይ ካየ ነው ከቁጥር የሚያስገባው። ዘጠኝ ክፍሎች ያሉት ይህ ተከታታይ ፊልም ባለፈው መስከረም ለዕይታ የበቃ ሲሆን በብድር የተዘፍቁ ሰዎች ስብስብ የሕፃናት ጨዋታ ሲጫወቱ ያሳያል።

ጨዋታውን ያሸነፈ ሰው በሚሊዮን ዶላሮች የሚያሸንፍ ሲሆን የተሸነፉ ሰዎች ደግሞ ዕጣ ፈንታቸው ሞት ይሆናል።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish