Home Entertainment News ፌስቡክ በሦስት ወራት ውስጥ 9 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አገኘ

ፌስቡክ በሦስት ወራት ውስጥ 9 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አገኘ

by sam

ሾልከው በወጡ ዓለም አቀፍ ሰነዶች ስሙ በክፉ እየተነሳ የሚገኘው ግዙፉ የማኅበራዊ ሚዲያ ትስስር መድረክ ፌስቡክ በሦስተኛው ሩብ ዓመት ከተጠበቀው በላይ ገቢ ማስገባቱ ተሰምቷል።

የማኅበራዊ ሚዲያ ድርጅቱ ከሐምሌ እስከ ነሐሴ ባሉት ሦስት ወራት ውስጥ 9 ቢሊዮን ዶላር ትርፍ ያገኘ ሲሆን ይህም ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ ወቅት ከነበረው 7.8 ቢሊየን ዶላር ብልጫን ያሳየ ነው።

ሆኖም በቅርቡ ይፋ በተደረገው የአፕል አይ ኦኤ ስ 14 ሥርዓት (ኦፐሬቲንግ ሲስተም) ያደረገው ማሻሻያ ማስታወቂያዎችን ለተመረጡ ደንበኞች እንዳያደርስ እንቅፋት ሆኖበታል።

ፌስቡክ ይህንን ገቢ ያገኘው በቀድሞ ሠራተኛው አማካኝነት የወጣበትን ሰነድ ተከትሎ ትችት እየተሰነዘረበት ባለበት ወቅት።

በፍራንሲስ ሃውገን በኩል ሾልኮ ለመገናኛ ብዙኃን የደረሰው ሰነድ ፌስቡክ ከተጠቃሚዎቹ ደኅንነት በላይ ትርፉን እንደሚያስቀድም ያትታል።

በርካታ ዘገባዎች ፌስቡክ ከአሜሪካ ውጭ የጥላቻ ንግግርን እና የወሲብ ንግድን የሚያበረታቱ ይዘቶችን በመደበኛነት መቆጣጠር እና ማስተካከል እንዳልቻለ አሳይተዋል።

ትላንት የፌስቡክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ማርክ ዙከርበርግ ከኢንቬስተሮች ጋር በነበራቸው ምክክር ላይ “የምናያቸው የሾለኩ ሰነዶችን ሆን ተብሎ የድርጅታችንን የውሸት ምስል ለማላበስ የሚደረግ የተቀናጀ ጥረት ነው” ብለዋል።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish