Home Entertainment News ምድር ከምትገኝበት ጋላክሲ ውጭ የመጀመሪያዋ የተባለች ‘ፕላኔት’ ተገኘች

ምድር ከምትገኝበት ጋላክሲ ውጭ የመጀመሪያዋ የተባለች ‘ፕላኔት’ ተገኘች

by sam

ምድር በምትገኝበት ጋላክሲ ውጭ የመጀመሪያዋ ፕላኔት ልትሆን የምትችል አካል መገኘቷን የስነ ሕዋ ጥናት ባለሙያዎች አስታውቀዋል።

እስካሁን ድረስ 5 ሺህ የሚሆኑ ‘ኤክሶፕላኔት’ የሚሰኙ አካላት ከጸሃይ ባሻገር የሚገኙ ሲሆን ሁሉም ግን የሚገኙት ‘ሚልኪዌይ’ በሚሰኘው ጋላክሲ ውስጥ ነው።

ፕላኔት ልትሆን ትችላለች የተባለችው አካል የተገኘችው በናሳው ቻንድራ ኤክስሬይ ቴሌስኮፕ ሲሆን የምትገኘውም ‘ሜሲዬ 51’ በሚሰኘው ጋላክሲ ውስጥ ነው።

ይህ ጋላክሲ ደግሞ ከሚልኪዌይ ጋላክሲ በ28 ሚሊየን የብርሀን ዓመታት ርቀት ላይ ነው የሚገኘው።

ዶክተር ሮሴን ዲ ስቴፋኖ እና የስራ ባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን ለረጅም ጊዜ የኤክስ ሬዮችን ብርሀንማ የመሆን ሂደት ሲከታተሉ የነበረ ሲሆን ከዚህ ብርሀን በተገኘ መረጃ ላይ ተመስርተው ነው አዲሷን ፕላኔት ማግኘት የቻሉት።

እስካሁን በተደረጉጉ ጥናቶችና በተገኙት መረጃዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ፕላኔት ልትሆን ትችላለች የተባለችው አካል ከሳተርን ጋር የሚቀራረብ መጠን እንዳላት እንደሚገመት ተመራማሪዎቹ ገልጸዋል።

ዶክተር ሮሴን እንደሚሉት እስከዛሬ ድረስ በሚልኪዌይ ጋላክሲ የሚገኙ አነስተኛ ፕላኔቶች ወይም ኤክሶፕላኔትስ ለማግኘት ጠቅም ላይ የሚውለው አሰራር በብዙ ጊዜ ውጤታማ አይሆንም።

ይህም የሚሆነው ባለው ከፍተኛ ርቀት ምክንኣት እንደሆነ ባለሙያዋ ያስረዳሉ።

ነገር ግን ኤክስ ሬይ በመጠቀም የሚደረገው አሰሳ የተሻለ ውጤት እንደሚያስገኝ ይገልጻሉ።

” በመላው የጋላክሲው ክፍል በአስርታት የሚቆጠሩ አካላት ተሰራጭተው እንደሚገኙ እናምናለን። በቀላሉም ልናገኛቸው እንችላለን። በተጨማሪም የእነዚህን አካላት አንዳንድ ክፍሎች በኢክስሬይ ሲታዩ ደመቅ ያሉ ናቸው። ርቀታቸውንና መጠናቸውንም መለካት እንችላለን”

ነገር ግን ተመራማሪዎቹ የማይክዱት አንድ ነገር አለ። እርግጠኛ ሆኖ ስለተገኘችው ፕላኔት መሰል አካል ለመናገር ተጨማሪ ምርምሮችና መረጃዎች እንደሚያስፈልጉ ነው።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish