Home Entertainment News ህንድ ውስጥ የተወለዱት መንትዮች ኮሮናና ኮቪድ የሚል ስም ተሰጣቸው።

ህንድ ውስጥ የተወለዱት መንትዮች ኮሮናና ኮቪድ የሚል ስም ተሰጣቸው።

by sam

ህንድ ውስጥ በምትገኘው ማዕከላዊዋ የቻቲስጋር ክልል ውስጥ የሚኖሩ ጥንዶች፣ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ የመላው ሃገሪቱ እንቅስቃሴ በታገደበት ወቅት፣ አዲስ የተወለዱ መንትያ ልጆቻቸውን ኮሮና እና ኮቪድ19 ብለው ሰይመዋቸዋል።

ህንድ ውስጥ የተወለዱት መንትዮች ኮሮናና ኮቪድ የሚል ስም ተሰጣቸው።

ህንድ ውስጥ በምትገኘው ማዕከላዊዋ የቻቲስጋር ክልል ውስጥ የሚኖሩ ጥንዶች፣ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ የመላው ሃገሪቱ እንቅስቃሴ በታገደበት ወቅት፣ አዲስ የተወለዱ መንትያ ልጆቻቸውን ኮሮና እና ኮቪድ19 ብለው ሰይመዋቸዋል።

ሴት እና ወንድ መንትዮቹ የተወለዱት፣ በክልሉ ዋና ከተማ ሬይፑር ውስጥ በሚገኝ አንድ የመንግስት ሆስፒታል ውሰጥ፣ እንቅስቃሴን የሚገድበው አዋጅ በወጣ በሁለተኛው ቀን ማለትም ማርች 27 ቀን ነበር።

የተገላገልኳቸው ከብዙ ውጣ ውረድ እና ችግር በኋላ በመሆኑ፣ እኔና ባለቤቴ ይህንን እለት የማይረሳ ማድረግ ፈለግን፣በማለት 27 አመቷ እናት ፕሪቲ ቬርማ ለህንድ የዜና ወኪል ፕሬስ ትረስት ተናግራለች።

ስያሜዎቹ በዚህ እገዳ ወቅት እና በመንግስት ሆስፒታል ውስጥ ባለፈው ሳምንት በሰላም ወሊድ ከመፈፀሟ በፊት የተጋፈጧቸውን ፈተናዎች እንደሚያስታውሷቸው ጥንዶቹ ገልፀዋል።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish