Home Sport News አትሌት ለተሰንበት የ”ሞመንት ኦፍ ዘ መንዝ” አሸናፊ ሆነች

አትሌት ለተሰንበት የ”ሞመንት ኦፍ ዘ መንዝ” አሸናፊ ሆነች

by sam

አትሌት ለተሰንበት ግደይ መስከረም 27፣2013 ዓ.ም ስፔን ቫሌንሺያ ተካሂዶ በነበረው የ5 ሺህ ሜትር ውድድር ክብረወሰን ማሻሻሏን ተከትሎ የፈረንጆቹ ኦክቶበር ወሩ አሸናፊ ተብላለች፡፡

የ22 ዓመቷ ለተሰንበት ርቀቱን ለማጠናቀቅ የፈጀባት ጊዜ 14 ደቂቃ ከ6 ሰከንድ ከ62 ማይክሮሰከንድ መሆኑ ይታወሳል፡፡

ይህን ተከትሎም በሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ተይዞ የነበረውን የሴቶች የ5 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰን ማሻሻል ችላ ነበር፡፡

ከዚህ ቀደም ከ12 ዓመታት በፊት በ14 ደቂቃ ከ11 ሰከንድ ከ15 ማይክሮሰከንድ በሆነ ጊዜ ጥሩነሽ ዲባባ የርቀቱ ክብረ ወሰን ባለቤት እንደነበረች ይታወሳል፡፡

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish