Home Entertainment News ሳሙዔል ኤቶ መኪና አደጋ አጋጠመው

ሳሙዔል ኤቶ መኪና አደጋ አጋጠመው

by sam

አራት ጊዜ የአፍሪካ የአመቱ ምርጥ ተጫዋች የሚለውን ማዕረግ የተቀዳጀው ሳሙኤል ኤቶ እሁድ እለት የመኪና አደጋ እንዳጋጠመው ተሰማ።

እንደ ሳሙኤል ኤቶ ቤተሰቦች ከሆነ ወደ ካሜሮን የንግድ ከተማ ዶኡላ በሚያመራበት ወቅት ነው የመኪና አደጋ ያጋጠመው።

ሳሙኤል በካሜሮን ምዕራባዊ ክፍል ከምትገኘው ባፎሳም ከተማ የሳምንቱ መጨረሻ ላይ የተካሄደን ፌስቲቫል ተካፍሎ እየመጣ እንደነበር ተገልጿል።

ሳሙዔል የነበረበትን መኪና የሚያሽከረክረው ሹፌር መኪናውን መቆጣጠር እንዳልቻለ እና ሌሎች  ሁለት መኪኖችን መግጨቱ ታውቋል።

ቤተሰቦቹ ሳሙኤል ኤቶ ወዲያውኑ ወደ ሆስፒታል መወሰዱን ጨምረው ተናግረዋል።

የእግር ኳሰኛው ቃል አቀባይ ለቢቢሲ ፒጅን እንደተናገሩት ኤቶ የነበረበት መኪና  ቢጎዳም እርሱ ግን በጥሩ ጤንነት ላይ ይገኛል።

ቃል አቀባዩ ከዚህ ውጪ ማንኛውንም ጥያቄ ለመቀበል ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish