Home Sport News የካፍ ፕሬዚዳንት አሕመድ አህመድ የአምስት አመት እግድ ተላለፈባቸው

የካፍ ፕሬዚዳንት አሕመድ አህመድ የአምስት አመት እግድ ተላለፈባቸው

by sam

ዓለም አቀፉ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል (ፊፋ) በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ፕሬዚዳንት አሕመድ አህመድ ላይ የአምስት አመት እገዳ አስተላለፈ፡፡ ፊፋ ፕሬዚዳንቱ ከገንዘብ እና ብልሹ አሰራር ጋር በተያያዘ ጥፋተኛ ናቸው ብሏል፡፡

የፊፋ የስነ ምግባር ኮሚቴም አህመድ አህመድ ከታማኝነት እና ከጥቅም ጋር የተያያዙ ደንቦችን ጥሰዋል ነው ያለው፡፡ከዚህ ጋር ተያይዞም ፕሬዚዳንቱ ላይ የአምስት አመት እግድ አስተላልፏል፡፡

የ60 ዓመቱ አህመድ አህመድ ከፈረንጆቹ 2017 ጀምሮ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽንን በፕሬዚዳንትነት ሲመሩ ቆይተዋል፡፡

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish