Home Sport News አትሌት ለተሰንበት ግደይ ለ2020 የዓለም አትሌቲክስ ሽልማት በሴቶች ዘርፍ ከታጩ አምስት አትሌቶች አንዷ ሆነች

አትሌት ለተሰንበት ግደይ ለ2020 የዓለም አትሌቲክስ ሽልማት በሴቶች ዘርፍ ከታጩ አምስት አትሌቶች አንዷ ሆነች

by sam

አትሌት ለተሰንበት ግደይ ለ2020 የዓለም አትሌቲክስ ሽልማት በሴቶች ዘርፍ ከታጩ ተመራጮች አንዷ መሆኗን የዓለም አትሌቲክስ አስታወቀ። 

ለተሰንበት ለሽልማቱ የታጨችው የ5 ሺህ ሜትር ርቀትን 14:06.62 በሆነ ጊዜ በመግባት የዓለም ክብረ-ወሰን በመስበሯ እና በዚሁ ርቀት ሞናኮ ውስጥ በተካሄደው የዋንዳ ዲያመንድ ሊግ ላይ ሁለተኛ ደረጃ ይዛ በማጠናቀቋ ነው። 

የ2020 የዓለም አትሌቲክስ ሽልማት እ.አ.አ ታኅሣሥ 5 ቀን 2020 በበይነ መረብ ታግዞ እንደሚካሄድ ተገልጿል። 

ዝግጅቱም በዓለም አትሌቲክስ የዩቲዩብ ቻናል እና በፌስቡክ ገጹ በቀጥታ የሚተላለፍ ይሆናል። 

ለሽልማቱ የታጩት ሌሎች አትሌቶች፣ ለኔዘርላንድስ የምትሮጠው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሲፈን ሐሰን (በሩጫ)፣ ኬንያዊቷ ፔሬዝ ጄፕቺርቺር (በሩጫ)፣ ቬኒዙዌላዊቷ ዩሊማር ሮጃስ (በዝላይ) እንዲሁም ጃማይካዊቷ ኤላይን ቶምፕሰን-ሔራህ (በሩጫ) ናቸው። 

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish