Home Sport News በዴልሂ ግማሽ ማራቶንን ኢትዮጵያዊያን አትሌቶቻችን በሁለቱም ፆታዎች ድል አደረጉ

በዴልሂ ግማሽ ማራቶንን ኢትዮጵያዊያን አትሌቶቻችን በሁለቱም ፆታዎች ድል አደረጉ

by sam

በህንድ ወርቅ ደረጃ በተሰጠው የዴልሂ ግማሽ ማራቶን ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች  በሁለቱም ጾታ ድርብ ድል ማስመዝገብ ችለዋል።

በወንዶች የግማሽ ማራቶን ሩጫ አምደወርቅ ዋለልኝ 58:53 በመሮጥ አንደኛ ሲወጣ የቦታውን ሰአት በማሻሻል አሸንፏል።

በውድድሩ ሌላኛው አትሌት አንዱ አምላክ በልሁ 2ኛ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ በግማሽ ማራቶን የተሳተፈው አትሌት ሙክታር ኢድሪስ 4ኛ ደረጃ አግኝቷል።

እንዲሁም በሴቶች ዘርፍ ያለምዘርፍ የኃለው ግማሽ ማራቶኑን በ64:46 ጊዜ በመግባት የቦታውን ሰአት ጭምር በማሻሻል አሸንፋለች።

በውድድሩ ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት አባብል የሻነው 3ኛ ደረጃን መያዟን ኢንዲያን ዶት ኮም ዘግቧል።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish