Home Sport News የ2013 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተጀምሯል

የ2013 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተጀምሯል

by sam

የ2013 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መክፈቻ ጨዋታ ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም ሲጀመር ድሬዳዋ ከተማ ከሰበታ ከተማ 0ለ0 ተለያይተዋል።

የፕሪሚየር ሊጉ የዛሬ ሁለተኛ ጨዋታ 9:00 ሰዓት ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከፋሲል ከነማ ጋር እንደሚጫወቱ የወጣው መርሐ ግብር ያስረዳል።

የሊጉ መርሐ ግብር ነገ እና ከነገ በስቲያ ሲቀጥል እሁድ ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ኢትዮጵያ ቡና ከወልቂጤ ከተማ ከቀኑ 9:00 ሰዓት ላይ ደግሞ ጅማ ከተማ ከአዳማ ከተማ ጋር ይጫወታሉ።

የፊታችን ሰኞ ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ላይ ወላይታ ድቻ ከሀዲያ ሆሳዕና እንዲሁም 9:00 ሰዓት ላይ ባህር ዳር ከተማ ከሲዳማ ቡና ጋር እንደሚጫወቱ ይጠበቃል።

ሁሉም ጨዋታዎች በአዲስ አበበ ስታዲየም የሚካሄዱ ይሆናል።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish