Home Sport News ሊዮኔል ሜሲ በፔሌ ተይዞ የነበረውን ለአንድ ክለብ በርካታ ግቦችን የማስቆጠር ክብረወሰን ሰበረ

ሊዮኔል ሜሲ በፔሌ ተይዞ የነበረውን ለአንድ ክለብ በርካታ ግቦችን የማስቆጠር ክብረወሰን ሰበረ

by sam

 ሊዮኔል ሜሲ በፔሌ ለሳንቶስ ክለብ 643 ግቦችን በማስቆጠር ይዞት የነበረውን ከፍተኛ ግብ አግቢነት ክብረወሰን ወደ 644 በማድረስ አሻሽሎታል፡፡

አርጅንቲናዊው አንድሬስ ሊዮኔል ሜሲ በፔሌ እ.ኤ.አ ከ1956 እስከ 1974 ባሉት 19 የውድድር ወቅቶች ነበር ለሳንቶስ 643 ግቦችን በማስቆጠር በዓለም ለአንድ ክለብ ከፍተኛ ግብ በማስቆጠር ክብረ ወሰኑ በእጁ ይዞ የነበረው፡፡

ባርሴሎና በላሊጋላው ትላንት ሪያልቫላዶሊድን 3ለ0 በረታበት ጨዋታ ሜሲ አንድ ግብ በማስቆጠሩ ለክለቡ ያስቆጠራቸው ግቦች ብዛት ወደ 644 ማድረስ ችሏል፡፡

ሜሲ ለባርሴሎና የመጀመሪያዋን ግብ ማስቆጠር የቻለው በ2005 ሲሆን አስር የላሊጋ አራት የቻምፒየንሰ ሊግ ዋንጫዎችን ማንሳት ችሏል፡፡

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish