Home Sport News ክርስቲያኖ ሮናልዶ የዓለማችን የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሆነ

ክርስቲያኖ ሮናልዶ የዓለማችን የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሆነ

by sam

ክርስቲያኖ ሮናልዶ በእግር ኳስ ታሪክ 760 ግቦችን በማስቆጠር የዓለማችን የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ክብረሰወሰንን ለመያዝ ችሏል።

የዘንድሮውን የጣልያን ሴሪአ በ15 ግቦች ከፍተኛ ግብ አግቢነቱን እየመራ ያለው የ34 ዓመቱ ሮናልዶ በቅርቡ ነበር ብራዚላዊውን ፔል ያስቆጠራቸው 757 ግችን መብለጥ የቻለው።

ክለቡ ጁቬንቱስ ትላንት ናፖሊን 2ለ0 በመርታት የጣልያን ሱፐርካፕ ዋንጫን ለ9ኛ ጊዜ ሲያነሳ ሮናልዶ አንዷን ግብ ማስቆጠር ችሏል ሲል ስካይ ስፖርት ዘግቧል።

ቼክ ሪፑብካዊው ጆሴፍ ቢካን በ759 ግቦች 2ኛ፣ ብራዚላዊው ፔሌ በ757 ግቦች 3ኛ፣ ብራዚላው ሮማሪዮ በ743 ግቦች 4ኛ፣ አርጅንቲናዊው ሊዮኔል ሜሲ በ719 ግቦችን በማስቆጠር 5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish