Home Sport News ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በየወሩ በእንጦጦ ፓርክ የሚደረገውን የ5ኪ.ሜ. ውድድር በይፋ አስጀመረ፡፡

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በየወሩ በእንጦጦ ፓርክ የሚደረገውን የ5ኪ.ሜ. ውድድር በይፋ አስጀመረ፡፡

by sam

 የተሳታፊዎችን የሩጫ ውድድር ፍላጎትና ጤናማ አኗኗር ባህል የማድረግ ፍላጎት መጨመርን ታሳቢ በማድረግ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በየወሩ የሚካሄድ 5ኪ.ሜ. ውድድርን  እንደሚጀምር በዛሬው እለት በይፋ አስታውቋል፡፡

ውድድሩ በአዲሱ እና ለስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ተስማሚ በሆነው የእንጦጦ ፓርክ ይካሄዳል፡፡ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ወር በገባ የመጀመሪያ ቅዳሜ በየወሩ የሚደረገው ይህ ውድድር የመጀመሪያው ዙር የፊታችን ጥር 29 ቀን 2013 ኣ.ም. ይካሄዳል፡፡

የዚህንም ፕሮግራም መክፈቻ ሃይሌ ገ/ስላሴ በተገኘበት ሳር ቤት በሚገኘው አዳምስ ፓቪልዮን አደባባይ ጋር በቅርብ ጊዜ እየተበራከቱ ከመጡትና የአካላዊ እንቅስቃሴ ባህልን እያዳበሩ ካሉ የተለያዩ የሩጫ ቡድኖች መካከል አንድ ከሆኑት ቡድኖች ጋር አብሮ በመሆን ከጠዋቱ 12:30 ጀምሮ ይደረጋል፡፡

የዚህ ውድድር ብቸኛ አጋር የሆነው በኮካ ኮላ አቅራቢነት በቅርብ ጊዜ ወደ ገበያ የገባው ፕሬደተር በልጠን እንድንገኝ የሚያስችለንን አዲስ ስሜት ረዘም ላለ ጊዜ የሚያላብስ ኃይል ሰጪ እና ከአልኮል ነፃ መጠጥ ነው።

ይህ ወራዊ ውድድር በየወሩ 200 ተሳታፊዎችን ብቻ ከክፍያ ነፃ የሚያስተናግድ ሲሆን ምዝገባም ውድድሩ ሊካሄድ አንድ ሳምንት ሲቀረው በየወሩ የሚደረግ ይሆናል፡፡ የመጀመሪያው ወር ምዝገባም በታላቁ ሩጫ ድህረ ገፅ በኩል ብቻ greatethiopianrun.com በጥር 17 ቀን 2013 ዓ.ም. ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡  

ስለ ውድድሩ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ እስትራቴጂክ እና ኢኖቬሽን ማኔጀር የሆኑት ዳግማዊት አማረ እንዳሉት ’ኮካ ኮላ ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር በአጋርነት እና የስፖርት ቴክኖሎጂን ለተሳታፊዎች በማስተዋወቅ ረገድ የረጅም ጊዜ ባለድርሻ አካል ሲሆን፣ የዚህ የአዲሱ እንጦጦ ፓርክ ፕሬደተር ሩጫ የቀጣዩን አዲስ የዲጅታል ውጤት ማሳወቂያ መንገድ በማስተዋወቅ ቀደምት የሚሆን ውድድሮችን በማዘጋጀት አጋርነቱን ቀጥሏል’ ብለዋል፡፡

ሁሉም የውድድር ተሳታፊዎች የውድድር ሰአታቸውን ልክ ውድድሩ እንደተጠናቀቀ ማወቅ የሚችሉ ሲሆን ውድድሩ በየወሩ ከጠዋቱ 2፡30 የሚጀመር ይሆናል፡፡

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish