Home Sport News የአውሮፓ ሊጎች መረጃዎች !

የአውሮፓ ሊጎች መረጃዎች !

by sam

• የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ተከታታይ ድል በማስመዝገብ በ ሜሲ እና ግሪዝማን ግቦች አትሌቲክ ቢልባኦን 2 ለ 1 አሸንፈዋል ።

• ባርሴሎና የምሽቱን ድል ተከትሎ በላሊጋው አምስተኛ ተከታታይ ድላቸው ሆኗል ።

• ባርሴሎና ሪያል ማድሪድ በመብለጥ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጡ ከመሪው አትሌቲኮ ማድሪድ በአስር ነጥብ ርቀዋል ።

• የምሽቱን ጎል ተከትሎ ሜሲ በባርሴሎና ቤት 650ኛ ጎሉን ከመረብ አሳርፏል ።

• ግሪዝማን ከ አዲሱ የፈረንጆች ዓመት በኋላ ወደ ቀደመ አቋመ ሲመለስ በሰባት ጨዋታዎች አምስት ጎሎችም አስቆጥሮ ሶስት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል ።

• ቶተንሀም ተከታትይ ሽንፈትን ሲያስተናግዱ ምሽቱን በ ትሮሳርድ ብቸኛ ግብ በ ብራይተን ተሸንፈዋል ።

• ብራይተን በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያውን ድል በሜዳቸው ማሳካት ችለዋል ።

• ስፐርስ ባለፉት አስር የሊጉ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻሉት በሶስቱ ሲሆን በአራት ጨዋታዎች ላይ ሽንፈት ቀምሰዋል ።

  • የባርሴሎና የጨዋታ ጎሎች ከላይ በቪድዮው ላይ ተያይዟል ።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish