Home Sport News ‘ሴቶች ብዙ ያወራሉ’ ያሉት የቶክዮ ኦሊምፒክ ኃላፊ ይቅርታ ጠየቁ

‘ሴቶች ብዙ ያወራሉ’ ያሉት የቶክዮ ኦሊምፒክ ኃላፊ ይቅርታ ጠየቁ

by sam

የቶክዮ ኦሊምፒክስ አዘጋጅ ኪሚቲ ኃላፊ የሆኑት ግለሰብ ሴቶችን አስመልክተው በሰጡት አስተያየት ምክንያት ሥልጣናቸውን ሊለቁ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።

የ83 ዓመቱ ዮሺሮ ሞሪ ‘ምንም ሳያሰላስሉ’ ለሰጡት አስተያየት ይቅር በሉኝ ብለዋል ሲሉ የጃፓን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

የኮሚቲው ኃላፊ ‘ሴቶች በጣም ብዙ ያወራሉ፤ ሴት የቦርድ ኃላፊዎች ያሉበት ስብሰባ በጣም ብዙ ጊዜ ይወስዳል’ ሲሉ ተናግረዋል ተብለው ተወቅሰዋል።

ረቡዕ በተካሄደው የጃፓን ኦሊምፒክ ኮሚቲ ስብሰባ ላይ ይህን ያሉት።

የኦሊምፒክ ኮሚቲው በአሁኑ ወቅት 24 አባላት ያሉት ሲሆን አምስቱ ሴቶች ናቸው።

የጃፖን ኦሊምፒክ ተሳታፊዎችን የመመረጥ ኃላፊነት ያለበት ይህ ኪሚቲ በፈረንጆቹ 2019 ሴት የቦርድ ኃላፊዎችን ድርሻ 40 በመቶ ለማድረስ ቃል ገብቶ ነበር።

“ሴት የቦርድ አባላትን ቁጥር ለመጨመር ካሰብን ለሚያደርጉት ንግግር የሚሰጣቸው ሰዓት የተወሰነ ሊሆን ይገባል። እነሱ እንደሆነ ቶሎ ተናግሮ የመጨረስ ችግር አለባቸው። በጣም ያናድዳል” ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል በማለት አሳሂ ሺምቡን ጋዜጣ ዘግቧል።

በፈረንጆቹ ከ2000 እስከ 2001 ለአንድ ዓመት ብቻ ጃፓን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ያስተዳደሩት ዮሪ ዲፕሎማሲ በራቃቸው አስተያየቶቻቸው ይታወቃሉ።

ሴቶችን በማስመልከት የሰጡት አስተያየትም ከማሕበራዊ ድር አምባ ተጠቃሚዎች ዘንድ ተቃውሞ አስነስቶባቸዋል።

በርካታ የትዊተር ተጠቃሚዎች ዮሪ ሥልጣን ይልቀቁ በማለት ላይ ናቸው።

ሰውዬው ቤት ሲገቡ ባለቤታቸው ጭምር በሰጡት አስተያየት እንደተቀየሟቸው መናገራቸውን አልደበቁም።

“ትላንት ምሽት ቤት ስገባ ባለቤቴ፤ አሁን ደግሞ ሌላ የማይሆን ነገር ተናገርክ አይደል? ሴቶችን የሚያፀይፍ ነገር በመናገርህ እኔ ነኝ የምሳቀቀው” ብለዋል።

“ዛሬ ጥዋት ደግሞ ሴት ልጄ፣ ሴት የልጅ ልጄ ወቀሳ ሰንዝረውብኛል” ብለዋል ሲል ጋዜጣው ዘግቧል።

የቶኪዮ ኦሊምፒክስ አዘጋጅ ኮሚቲ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ለአንድ ዓመት የዘገየውን የቶኪዮ ኦሊምፒክና ፓራሊምፒክ በተሳካ ሁኔታ ለማዘጋጀት ደፋ ቀና እያለ ይገኛል።

ኮሚቲው 36 ከፍተኛ የቦርድ አባላት ያሉት ሲሆን ከዚህ ቀድም ጃፓን ውስጥ በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ የሠሩ ናቸው።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish