Home Sport News ሉዊስ ሱዋሬዝ በ ባርሴሎና ያጋጠመውን ተናገረ !

ሉዊስ ሱዋሬዝ በ ባርሴሎና ያጋጠመውን ተናገረ !

by sam

በ ክረምቱ ከ ካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ተገፍቶ የወጣው ዩራጋዊው የፊት መስመር አጥቂ ሉዊስ ሱዋሬዝ በላሊጋው መሪ አትሌቲኮ ማደሪድ ደማቅ ጊዜን እያሳለፈ ይገኛል ።

ሉዊስ ሱዋሬዝ ሰፊ ሀሳቦችን ሲያነሳ በተለይም ከ ባርሴሎና ጋር የተለያየበትን መንገድ ተናግሮ አልፏል ።

” በ ባርሳ ልምምድ እንዳልሰራ ነግረውኝ ነበር ፣ ነገር ግን ኮንትራት እስካለኝ ድረስ ልምምድ መስራቴን እንደማላቆም ነገርኳቸው ።

ክለቡ ምንም ዓይነት ማብራሪያ አልሰጠኝም ፣ ይህ ውሳኔ የአዲሱ አሰልጣኝ ሮናልድ ኩማን ብቻ እንደሆነ ነግረውኛል ” ሲል ወቅቱን በማስታወስ አስተያየቱን ሰጥቷል ።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish