Home Sport News የአውሮፓ መረጃዎች !

የአውሮፓ መረጃዎች !

by sam

• ቼልሲ በ ኤ ፌ ካፑ ባርንስሌይን በታሚ አብርሀም ብቸኛ ጎል በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል ።

• ቶማስ ቱሄል ቼልሲን ከተረከቡ በኋላ አንድም ሽንፈት ያልቀመሱ ሲሆን ስድስት ጎሎችን አስቆጥረው አንድ ግብ ብቻ አስተናግደዋል ።

• ባየር ሙኒክ በ ቤንጃሚን ፓቫርድ ብቸኛ ግብ ታይገርስን በማሸነፍ የአለም የክለቦች ዋንጫን ማሸነፍ ችለዋል ።

• ሀንስ ፍሊክ ሌላ ዋንጫ ማሳካት ሲችሉ በ 68 ጨዋታዎች ስድስተኛው ዋንጫቸው ሆኗል ።

• ታሚ አብርሀም በዘንድሮው የውድድር ዓመት 1425 ደቂቃዎችን ተሰልፎ መጫወት ሲችል አስራ ሁለት ጎሎችን አስቆጥሮ ስድስት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል ።

• ባየር ሙኒክ ከ ባርሴሎና በመቀጠል ስድስት ዋንጫዎችን ከፍ ማድረግ የቻሉ ሁለተኛው ክለብ ሆነዋል ።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish