Home Sport News ትላንት ምሽት በስፔን ማድሪድ በተካሄደ የቤት ውስጥ የአትሌቲክስ ውድድር ኢትዮጵያን አትሌቶች በድል ተንበሻብሸዋል

ትላንት ምሽት በስፔን ማድሪድ በተካሄደ የቤት ውስጥ የአትሌቲክስ ውድድር ኢትዮጵያን አትሌቶች በድል ተንበሻብሸዋል

by sam

ትላንት ምሽት በስፔን ማድሪድ ከተማ በተካሄደ የቤት ውስጥ የአትሌቲክስ ውድድር ኢትዮጵያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል።

በሴቶች 3ሺህ ሜትር አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ በ8:22:65 አንደኛ በመውጣት የምንጊዜም ሁለተኛ ምርጥ ሰዓት በማስመዝገብ  በበላይነት ስታጠናቅቅ፣ ለምለም ኃይሉ በሁለተኛነት ውድድሯን አጠናቃለች።

በወንዶች 1500 ሜትር ደግሞ ሰለሞን ባረጋ 3:35:42 በመግባት በአንደኛነት አጠናቋል።

በተመሳሳይ በሴቶች 1500 ሜትር ሂሩት መሸሻ 4:09:42 በመግባት በሁለተኛነት አጠናቃለች።

በተጨማሪም፣ በሴቶች 800 ሜትር ሀብታም አለሙ የቦታውን ሰዓት ጭምር በማሻሻል 1:58:94 በመግባት በአንደኛነት ማጠናቀቋ የአፍሪካ አትሌቲክስ ዩናይትድ መረጃ ያመለክታል።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish