Home Sport News ፒኤስጂ እና ሊቨርፑል ቀጣዩን ዙር አልፈዋል !

ፒኤስጂ እና ሊቨርፑል ቀጣዩን ዙር አልፈዋል !

by sam

የፈረንሳዩ ሀያል ክለብ ምንም እንኳ በሜዳቸው አንድ አቻ ቢለያዩም በድምር ውጤት 5 ለ 2 ባርሴሎናን በማሸነፍ ቀጣዩን ዙር ተቀላቅለዋል ።

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ሌፕዚግን በ ሞሀመድ ሳላህ እና ሳድዮ ማኔ ግቦች በማሸነፍ በቀላሉ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል ። 

ከአስራ ስድስት ዓመታት በኋላ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ያለ ሜሲ እና ሮናልዶ የሚካሄድ ይሆናል ።

ዲያጎ ጆታ በዘንድሮው የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ አራት ጎሎችን ሲያስቆጥር አንድ ለግብ የሚሆን ኳስ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል ።

ሊዮኔል ሜሲ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ባደረጋቸው 149 ጨዋታዎች 120 ጎሎችን ከመረብ አዋህዷል ።

ሞሀመድ ሳላህ በሁሉም የውድድር መድረኮች ያስቆጠራቸውን የግብ መጠን ወደ ሀያ አምስት አሳድጓል ።

ምባፔ በ ሻምፒየንስ ሊጉ ያገባቸውን የግብ መጠን ወደ ስድስት ከፍ ሲያደርግ የኮከብ ግብ አግቢነቱን በሁለተኝነት እየመራ ይገኛል ።

ምባፔ በ አውሮፓ ሻምፒየንስ ሊጉ በድምሩ አርባ ሁለት ጨዋታዎችን ሲያካሂድ በ አርባ ጎሎች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎን ማድረግ ችሏል ።

ኬለር ናቫስ የ ሜሲን ፍፁም ቅጣት ምት ጨምሮ ስምንት ንፁህ ኳሶችን በመጀመሪያው አጋማሽ አድኗል ።

ሊዮኔል ሜሲ በሻምፒየንስ ሊጉ ፍፁም ቅጣት ምት ሲስት ከ ስድስት ዓመታት በኋላ የመጀመሪያው ነው ።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish