Home Sport News በቻምፒየንስ ሊጉ ሪያል ማድሪድ እና ማንቼስተር ሲቲ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀሉ

በቻምፒየንስ ሊጉ ሪያል ማድሪድ እና ማንቼስተር ሲቲ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀሉ

by sam

 በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ትናንት ምሽት ሁለት ጨዋታዎች ተካሄደዋል፡፡

ማንቼስተር ሲቲ ቦሩሲያ ሞንቼግላድባህን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ባሸነፈበት ጨዋታ፥ ኬቪን ደብሩይነ እና ኢካይ ጉንዶኻን የድል ጎሎቹን አስቆጥረዋል፡፡

በደርሶ መልስ ውጤት ማንቼስተር ሲቲ 4 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል፡፡

በሌላ ጨዋታ ሪያል ማድሪድ አታላንታን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

ካሪም ቤንዜማ፣ ሰርጂዮ ራሞስ እና ማርኮ አሴንሲዮ የማሸናፊያ ጎሎቹን ለሪያል ማድሪድ ሲያስቆጥሩ፥ ሙሪዬል ደግሞ ለአታላንታ የማስተዛዘኛ ጎሏን ማስቆጠር ችሏል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ሪያል ማድሪድ በደርሶ መልስ ውጤት 4 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የሩብ ፍጻሜ ተፋላሚ መሆኑን አረጋግጧል፡፡

ፒ ኤስ ጂ፣ ቦሩሲያ ዶርትመንድ፣ ሊቨርፑል እና ፖርቶ ቀደም ብለው ሩብ ፍጻሜውን መቀላቀላቸው ይታወሳል፡፡

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish