Home Sport News የጣልያን ሴርያ በአጓጊነቱ ቀጥሏል

የጣልያን ሴርያ በአጓጊነቱ ቀጥሏል

by sam

አታላንታ በ ሉካስ ሙሪየል ሁለት ጎሎች እና ዱቫን ዛፓታ አንድ ግብ ዩዲኒዜን 3 ለ 2 ማሸነፍ ችለዋል ።

ሙሪያል በውድድር ዓመቱ አስራ ስምንት ጎሎችን ሲያስቆጥር ከ ሉካኩ እና ሮናልዶ ብቻ ተብልጦ ይገኛል ።

ላዚዮ በመጨረሻው ደቂቃ ካይሲዶ ያስቆጠራት ግብ ነጥብ ከመጣል ስትታደጋቸው አዲስ አዳጊዎቹን ስፔዚያን 2 ለ 1 አሸንፈዋል ።

የስፔዚያን አቻ ያደረገች ግብ ያስቆጠረው ዳንኤል ቬርዲ ድንቅ የመቀስ ምት ከመረብ ማሳረፍ ችሏል ።

ሰባት ጎሎች በተቆጠሩበት መርሐ ግብር ናፖሊ በ ኢንሲኔ ፣ ኦሲሜን ፣ ሜርትንስ እና ሎሬንዞ ግቦች 4 ለ 3 ክሮቶኔን ማሸነፍ ችለዋል ።

በሌላ የሴርያው መርሐ ግብር ሳሱሎ እና ሮማ ሁለት አቻ በሆነ ውጤት መለያየት ችለዋል ።

በዛሬው ዕለት የተመዘገቡትን ውጤየ ተከትሎ ጁቬንቱስ ከደረጃ ሰንጠረዡ አራት ውስጥ ውጪ ሆነዋል ።

ጁቬንቱስ በደረጃ ሰንጠረዡ አምስተኛ ላይ ሲቀመጡ ከሰዓታት በኋላ በቱሪን ደርቢ ከ ቶሪኖ ጋር ጨዋታቸውን ያካሂዳሉ ።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish