Home Sport News ሰሜን ኮሪያ በኮቪድ19 ምክንያት በቶኪዮ ኦሊምፒክ እንደማትሳተፍ አስታወቀች

ሰሜን ኮሪያ በኮቪድ19 ምክንያት በቶኪዮ ኦሊምፒክ እንደማትሳተፍ አስታወቀች

by sam

ሰሜን ኮሪያ በኮቪድ 19 ምክንያት በጃፓኑ ቶኪዮ ኦሊምፒክ እንደማትሳተፍ አስታወቀች፡፡

ፒዮንግያንግ ከከቪድ19 ጋር ተያይዞ የአትሌቶችን ጤንነት ለመጠበቅ በማሰብ በውድድሩ እንደማትሳተፍ አስታውቃለች፡፡

ሰሜን ኮሪያ ታሪካዊ የተባለውን ውይይት ካደረገች በኋላ በ2018 በተዘጋጀው የክረምት ኦሊምፒክ ላይ 22 አትሌቶቿን ወደ ደቡብ ኮሪያ መላኳ ይታወሳል፡፡ 

የአሁኑ የሰሜን ኮሪያ ውሳኔ ታዲያ ደቡብ ኮሪያ ከዘወትር ባላንጣዋ ጋር ለመወያየት የሰነቀችውን ተስፋ የሚያጨልም ነው ተብሏል፡፡

የኪም ጆንግ ኡን አስተዳደር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በሀገሪቱ እንደሌለ በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል፡፡

የጤና ባለሙያዎች በአንጻሩ በሀገሪቱ ኮሮናቫይረስ አልተከሰተም የሚለው ነገር የማይሆን ነው  ብለዋል፡

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish