Home Sport News ማንችስተር ሲቲ ከሜዳቸው ውጪ ድል ቀንቷቸዋል

ማንችስተር ሲቲ ከሜዳቸው ውጪ ድል ቀንቷቸዋል

by sam

ሲቲዎች በ ፓርክ ደ ፕሪንስ ከመመራት ተነስተው በ ዴብሩን እና ማህሬዝ ጎሎች ፒኤስጂን 2 ለ 1 አሸንፈዋል ።

• ኢድሪስ ጋና ጉዬ በ ጉንዶጋን ላይ የሰራውን ከባድ ጥፋት ተከትሎ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል ።

• ሪያድ ማህሬዝ በ አውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ግብ ማስቆጠር የቻለው የመጀመሪያው አልጄሪያዊ ተጫዋች ሆኗል ።

• ኬቨን ዴብሩን በዘንድሮው የውድድር ዓመት በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ባደረጋቸው ስድስት ጨዋታዎች በሰባት ጎሎች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ አድርጓል ።

• አንጌል ዲ ማርያ በክለቡ ታሪክ ከ ሳፌት ሱሲች ጎን ለጎን ብዙ ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን ( 103 ) በማቀበል ቀዳሚው ተጫዋች ሆኗል ።

• ፒኤስጂን መሪ ያደረገች ግብ ያስቆጠረው ማርኪኖስ በ አውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ በእግር ኳስ ህይወቱ ያስቆጠረው ዘጠነኛ ጎሉ ሆኗል ።

• የማርኪኖስ ግብ በ አውሮፓ መድረክ ፒኤስጂዎች ያስቆጠሩት 446ኛ ጎል ሲሆን ከ ሊጉ ክለብ ሊዮን በታሪክ ቀዳሚው ክለብ አድርጓቸዋል ።

• ፒኤስጂ ባለፉት አስር በሜዳቸው ባደረጓቸው ጨዋታዎች ከሁለት መርሐ ግብሮች ውጪ በተቀሩት ግብ ተቆጥረውባቸዋል ።

• አንጌል ዲማርያ በዘንድሮው የውድድር ዓመት በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊጉ አራት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ሲያቀበል በሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል ።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish