Home Sport News ዩናይትድ ድል ሲቀናው አርሴናል ተሸንፏል

ዩናይትድ ድል ሲቀናው አርሴናል ተሸንፏል

by sam

ቀያይ ሴጣኖቹ ከመመራት ተነስተው ሮማን 6 ለ 2 ሲያሸንፉ ወደ ስፔን ያቀኑት መድፈኞቹ በ ቪያሪያል 2 ለ 1 ተሸንፈዋል ።

• ብሩኖ ፈርናንዴዝ በዘንድሮው የውድድር ዓመት ለቀያይ ሴጣኖቹ በሁለም የውድድር መድረኮች በ አርባ አንድ ጎሎች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ማድረግ ችሏል ።

• ብሩኖ ፈርናንዴዝ ሀያ አንድ የፍፁም ቅጣት ምቶችን ሲያገኝ የሳተው አንዱን ብቻ ነው ።

• ካቫኒ ካለፉት አምስት ጨዋታዎች መካካል በአምስቱ ግብ አስቆጥሯል ።

• ኤዲን ዜኮ ከ ማንችስተር ዩናይትድ ጋር ባደረገው አስር ጨዋታዎች ስምንተኛ ጎሉን ማስቆጠር ችሏል ።

• ካቫኒ በሮማ ላይ በድምሩ ያስቆጠራቸውን የግብ መጠን ወደ ዘጠኝ ከፍ አድርጎታል ።

• ዜኮ ካስቆጠራቸው ስምንት ጎሎች መካከል ስድስቱ በ ኦልድ ትራፎርድ ያስቆጠረው ናቸው ።

• ብሩኖ ፈርናንዴዝ በውድድር ዓመቱ ያስቆጠራቸውን የግብ መጠን ወደ ሀያ ስድስት ከፍ አድርጎታል ።

• ብሩኖ ፈርናንዴዝ በተከታታይ ሶስት የውድድር ዓመታት ሀያ አምስት እና ከዚያ በላይ ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል ።

• አርሴናል ዳኒ ሴባዮስን በሁለተኛው አጋማሽ በቀይ ካርድ አጥተዋል ።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish