የ ኮፓ አሜሪካን የሚያስተናግዱት ብራዚል የሀገሪቱ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሮጄርዮ ካቦክሎ በወሲባዊ ትንኮሳ ምክንያት በጊዜያዊነት መታገዳቸው ተሰምቷል ።
ሮጄርዮ የፌዴሬሽኑ ሰራተኛ ላይ ወሲባዊ ትንኮሳውን ሲፈፅሙ በድምጽ የተቀዱ ቅጅዎች በማስረጃነት መቅረባቸው ሙሉ ለ ሙሉ ከሀላፊነት እንዲታገዱ ሊያደርጋቸው እንደሚችል ተገልጿል ።
የ 82 ዓመቱ አንቶኒዮ ካርሎስ ኑኔዝ በጊዜያዊነት የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ሆነው እንደሚያገለግሉ ተነግሯል ።