Home Sport News ጣልያን አውሮፓ ዋንጫውን በድል ጀምራለች

ጣልያን አውሮፓ ዋንጫውን በድል ጀምራለች

by sam

የሮቤርቶ ማንሲኒ የድል ጉዞ ወደ ሀያ ስምንት ከፍ ባለበት መርሐ ግብር ጣልያን በ ዴሚራል ራሱ ላይ ፣ ኢንሲኜ እና ኢሞቢሌ ጎሎች ቱርክ ላይ ድል ተቀዳጅተዋል ።

• የጣልያን የተከላካይ ክፍል እምብዛም ባልተፈተነበት ጨዋታ ጂያንሉጂ ዶናሩማ መረቡን ሳያስደፍር ወጥቷል ።

• ኢሞቢሌ በ ጣልያን መለያ ያስቆጠራቸውን የግብ መጠን ወደ አስራ አራት ማድረስ ችሏል ።

• ዴሚራል በአውሮፓ ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታ በራሱ ላይ ግብ ያስቆጠረ በታሪክ የመጀመሪያው ተጫዋች ሆኗል ።

• ጣልያን በአውሮፓ መድረክ ውድድሮች ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ሶስት ጎሎችን ማስቆጠር ችለዋል ።

• ሎሬንዞ ኢንሲኜ ለጣልያን ባደረጋቸው ባለፉት አስራ ሁለት ጨዋታዎች በአስራ ሁለት ጎሎች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ አድርጓል ።

• ቱርክ ለአውሮፓ ዋንጫ ለማለፍ ባደረገቻቸው የማጣርያ ጨዋታዎች በሙሉ ሶስት ጎሎች ብቻ ሲቆጠርባቸው በዛሬው ዕለት ከወዲሁ በመክፈቻው ሶስት ጎሎች ሊቆጠርባቸው ችሏል ።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish