Home Entertainment News ከመቅደላ በዝርፊያ ወደ እንግሊዝ የተወሰዱ ቅርሶች በጨረታ እንዳይሸጡ ተደረገ

ከመቅደላ በዝርፊያ ወደ እንግሊዝ የተወሰዱ ቅርሶች በጨረታ እንዳይሸጡ ተደረገ

by sam

እንግሊዝ ውስጥ በሰኔ 10/2013 ዓ.ም በጨረታ ሊሸጡ የነበሩና ከመቅደላ የተዘረፉ ሁለት ቅርሶች ሽያጭ መቆሙ ተገለጸ።

ጨረታውን ያወጣው የእንግሊዙ በስቢ ኦክሽነርስና ቫሉወርስ የተባለ የጨረታ ድርጅት ሲሆን በእንግሊዝ ያለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከድርጅቱ ኃላፊዎች ጋር ያደረገው ውይይትን ተከትሎ ነው ጨረታው እንዲንዲቋረጥ የተደረገው።

የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባወጣው መግለጫ በጨረታ ሊሸጡ የነበሩት ቅርሶች ጥንታዊ መጽሐፍ ቅዱስ ከነ ማኅደሩና መስቀል እንዲሁም ፅዋዎች መሆናቸውን አስታውቋል።

እነዚህ ቅርሶች በመቅደላ ጦርነት ወቅት ዘምተው ከነበሩት የእንግሊዝ ወታደሮች መካከል በጄኔራል ዊልያም አርቡትኖት አማካኝነት የተዘረፉ ናቸው።

በመቅደላ ወቅት የተዘረፉ ቅርሶችን ለማስመለስ እየተደረገ ካለው ጥረት ጋር ተያይዞም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለበስቢ ይፋዊ በሆነ ደብዳቤ ቅርሶቹ ከሽያጩ እንዲወጡ የጠየቀው ባለፈው ሳምነት ነበር። ከዚህም በተጨማሪ ቅርሶቹንም ወደ ኢትዮጵያ የሚመለሱበትን ሁኔታ ድርጅቱ እንዲተባበርም ተጠይቋል።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish