Home Entertainment News በጁዶ ስልጠና 27 ጊዜ ወደ መሬት የተጣለው የታይዋን ታዳጊ ሞተ

በጁዶ ስልጠና 27 ጊዜ ወደ መሬት የተጣለው የታይዋን ታዳጊ ሞተ

by sam

በታይዋን ጁዶ በተባለው ራስ የመከላከል ሰፖርት አይነት 27 ጊዜ ከአየር ወደ መሬት የተጣለው የ7 አመት ታዳጊ ህይወት አልፏል።

በሚያዝያ ወር ላይ ህፃኑ በጁዶ ስልጠና ወቅት አብሮት የሚማር ታዳጊና አሰልጣኘ ከአየር ላይ ወደ መሬት ማጣጋታቸውን ተከትሎ ጭንቅላቱ ደም መፍሰስ አጋጥሞታል ተብሏል።

ስሙ ያልተጠቀሰው ይህ ታዳጊ ራሱን ስቶ በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ በአጋዥ መሳሪያ እየታገዘ ይተነፍስ ነበር።

ከ70 ቀናት በሆስፒታል ቆይታም በኋላ ቤተሰቦቹ አጋዥ መሳሪያው እንዲነቀል ውሳኔ ላይ መድረሳቸውን የአገሪቱ ሚዲያ ታይፔይ ታይምስ ዘግቧል።

ሆ የተባሉት አሰልጣኝ ልጁ ሆስፒታል እንደገባ በቁጥጥር ስር ውለው የነበረ ቢሆንም ከሳምንታት በፊት በ3 ሺህ 583 ዶላር ዋስ ወጥተው ነበር።

በአሁኑ ወቅት ታዳጊው መሞቱን ተከትሎ አቃቤ በመጀመሪያ ያቀረበውን ክስ በመቀየር “ወደ ሞት የሚያደርስ አደጋ በሚል” እንደሚቀይረውም ታይዋን ኒውስ የተባለ የዜና ወኪል ዘግቧል።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish