Home Entertainment News የፒካሶ ሥዕል ከተሰረቀ ከዓመታት በኋላ አቴንስ ውስጥ ተገኘ

የፒካሶ ሥዕል ከተሰረቀ ከዓመታት በኋላ አቴንስ ውስጥ ተገኘ

by sam

ከዘጠኝ ዓመታት በፊት ግሪክ ከሚገኝ የስዕል ማሳያ ጋለሪ የተሰረቀው የፓብሎ ፒካሶ ሥዕል ተገኘ፡፡

የአቴንስ ፖሊሶች ሰኞ ዕለት እንደገለጹት የፒካሶ ‘የሴት ራስ’ (Woman’s Head) የተሰኘው ሥራ በ አውሮፓውያኑ 1905 በፒየት ሞንድሪያን ከተሳለው የዊንዲሚል (windmill) ሥዕል ጋር ተገኝቷል፡፡

ሁለቱም ስዕሎች ከሌላ አንድ የጥበብ ውጤት ጋር ከአቴንስ ብሔራዊ ጋለሪ እአአ 2012 በተፈጸመ ሰፊ ስርቆት ተወስደዋል፡፡

የጥበብ ሥራዎቹ ከተሰቀሉበት ለመውሰድ ደቂቃዎችን ብቻ ነበር የወሰደባቸው፡፡

ሮይተርስ የዜና ወኪል ስማቸው ያልተገለጸ የፖሊስ ባለሥልጣንን በመጥቀስ የጥበቡ ሥራው ከአቴንስ ዳርቻ በሚገኝ ገደል ተደብቆ መገኘቱን እና አንድ ግሪካዊው በቁጥጥር ስር መዋሉን ዘግቧል፡፡

የመገኘቱ ዜና ይፋ የተደረገው የግሪክ ፖሊስ የጥበብ ሥራው በሃገሪቱ ውስጥ ነው ብሎ እንደሚያምን ከተዘገበ ከወራት በኋላ ነው፡፡

የፒካሶ ሥዕል እአአ በ 1949 በሰዓሊው ለብሔራዊ ስዕል ማዕከሉ የተሰጠ ነው፡፡

ከአስር ዓመታት በፊት የሳለውን ስዕል የሰጠው ሃገሪቱ ናዚ ጀርመንን ለመመከት ላደረገችው ትግል ዕውቅና ለመስጠት ነው።

በስርቆቱ ወቅት ዘራፊዎቹ ከቦታው ጥለው ሲያመልጡ ሁለተኛው የሞንደርያን ሥዕል የወደቀበት ቦታ ጥለውት ሸሽተዋል፡፡

ባለሥልጣናቱ ማክሰኞ ዕለት ስለ ኪነ-ጥበባት ሥራ መገኘት ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish