Home Entertainment News ዝነኛው የፊልም ተዋናይ አሌክ ባልድዊን በቀረጻ ወቅት ተኩሶ ሰው ገደለ

ዝነኛው የፊልም ተዋናይ አሌክ ባልድዊን በቀረጻ ወቅት ተኩሶ ሰው ገደለ

by sam

ዝነኛው አሜሪካዊ ተዋናይ አሌክ ባልድዊን በፊልም ቀረጻ ወቅት ለቀረጻ ተብሎ የተዘጋጀ መሳሪያ ተኩሶ አንዲት ሴትን ገደለ።

ተዋናይ አሌክ ባልድዊን በፊልም ቀረጻ ወቅት መደበኛ የጦር መሣሪያ ያልሆነ፣ ለፊልም ቀረጻ የሚያገለግል መሳሪያ ከተኮሰ በኋላ አንዲት ሴትን ገድሎ ሌላ አንድ ተጨማሪ ሰው አቁስሏል።

ፖሊስ እንዳለው ባልድዊን መሣሪያውን የተጠቀመው ለሴንቸሪ ዌስተርን ረስት ፊልም በሚቀረጽበት ወቅት ነው።

ጉዳት የደረሰባት ሴት ሆስፒታል ብትወሰድም በደረሰባት ጉዳት ህይወቷ አልፏል። ጉዳት ያጋጠመው የፊልሙ ዳይሬክተር ሕክምና እየተደረገለት ይገኛል።

የተዋናይ ባልድዊን ቃል አቀባይ ለኤፒ የዜና ወኪል እንደተናገረው ክስተቱ የተፈጠው ባዶ መሆን የነበረበት መደበኛ ያልሆነው መሳሪያ በስህተት ከተተኮሰ በኋላ ነው።

ህይወቷ ያለፈው የ42 ዓመቷ ሃልይና ሁትቺንስ የምትባል ሲሆን የፎቶግራፍ ዳይሬክተር ሆና ታገለግል ነበር ተብሏል። ህክምና እየተደረገለት ያለው የፊልሙ ዳይሬክተር የ48 ዓመቱ ዮኤል ሱዛ ነው።

ዝነኛ በሆነው የፊልም ቀረጻ ሥፍራ ቦናንዛ ክሪክ ራንች ስለተፈጠረው ክስተት ፖሊስ ምርመራውን እያካሄደ ሲሆን እስካሁን ምንም ክስ አልተመሰረተም።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish