Home Sport News አትሌት ለተሰንበት ግደይ በቫሌንሺያ ግማሽ ማራቶን ክብረወሰን በመስበር አሸነፈች

አትሌት ለተሰንበት ግደይ በቫሌንሺያ ግማሽ ማራቶን ክብረወሰን በመስበር አሸነፈች

by sam

 በስፔን ቫሌንሺያ ላይ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር የተሳተፈችው ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ለተሰንበት ግደይ 1 ሰዓት ከ02 ደቂቃ ከ52 ሰኮንድ በመግባት የቦታውን ክብረወሰን በመስበር አሸነፈች።

በውድድሩ አትሌት ለተሰንበትን ተከትላ ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው ሁለተኛ ወጥታለች።

የቫሌንሺያ ግማሽ ማራቶን ክብረወሰን ከዚህ በፊት በኬንያዊቷ ኪቢዎት ካንዲ የተያዘ ነበር፡፡ 

አትሌት ለተሰንበት በአሁኑ ወቅት የዓለም 5 ሺህ ሜትር እና 10 ሺህ ሜትር ክብረወሰኖች ባለቤት ናት። 

ዛሬ ቫሌንሺያ ላይ በተካሄደው ውድድር አንደኛ የወጣችው አትሌት ለተሰንበት ያመጣችው ውጤት በውድድሩ አዘጋጆች ተጣርቶ ኦፊሴላዊ ሆኖ እስኪወጣ እየተጠበቀ ነው።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish