Home Sport News በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮኑ ሊቨርፑል ከኤቨርተን ጋር ሁለት አቻ ተለያየ

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮኑ ሊቨርፑል ከኤቨርተን ጋር ሁለት አቻ ተለያየ

by sam

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 5ኛ ሳምንት መርሐ ግብር የአምናው ሻምፒዮን ሊቨርፑል በዘንድሮው የውድድር ዓመት ሊጉን በ12 ነጥቦች እየመራ ከሚገኘው ኤቨርተን ጋር ሁለት አቻ ተለያይቷል። 

ሊቨርፑል በመጀመሪያ የጫወታ ክፍለ ጊዜ በ3ኛው ደቂቃ ላይ ሳዲዮ ማኔ ባስቆጠራት ግብ መሪ መሆን ቢችልም ማይክል ኪን ለኤቨርተን በ19ኛው ደቂቃ የአቻነቷን ግብ አስቆጥሮ በአንድ አቻ ውጤት ወደ መልበሻ ክፍል ገብተዋል፡፡

ከእረፍት መልስ መሐመድ ሳላህ በ72ኛው ደቂቃ ለሊቨርፑል 2ኛዋን ግብ ሲያስቆጥር ከ9 ደቂቃዎች በኋላ ፕሪየር ሊጉን በኮከብ ግብ አግቢነት እየመራ ያለው የኤቨርተኑ ዶሚኒክ ካልቨርት ሌዊን ሁለኛዋን እና የአቻነቷን ግብ በግንባሩ በግሩም ሁኔታ ማስቆጠር ችሏል። 

ጨዋታው ሊጠናቀቅ ሲል ሊቨርፑል በጆርዳን ሄንደርሰን አማኝነት 3ኛዋን ግብ ቢያስቆጥርም በምስል በታገዘ ዳኝነት (VAR) ግቡ ከጫወታ ውጭ በመሆኑ ተሸሯል፡፡ 

ጨዋታውም ሁለት አቻ በመጠናቀቁ ኤቨርተን በ5 ጨዋታዎች በሰበሰበው 13 ነጥቦች የሊጉን መሪነት አጠናክሮ ቀጥሏል። 

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish