Home Sport News ኢትዮጵያ በዓለም የግማሽ ማራቶን ሻምፒዮና በሴቶች በቡድን ውጤት 1ኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቀቀች

ኢትዮጵያ በዓለም የግማሽ ማራቶን ሻምፒዮና በሴቶች በቡድን ውጤት 1ኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቀቀች

by sam

በፖላንድ በተካሄደው በዓለም የግማሽ ማራቶን ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በሴቶች በቡድን 1ኛ ደረጃ በመያዝ የወርቅ ተሸላሚ ሆናለች። 

በወንዶች የቡድን ውጤት ደግሞ የብር ሜዳልያ በማግኘት በአጠቃላይ በውድድሩ ከዓለም ኬንያን ተከትላ 2ኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች።

በሻምፒናው በጠቅላላ ውጤት ኬኒያ 1ኛ፣ ኢትዮጵያ 2ኛ፣ ኡጋንዳ 3ኛ ሆነው ሲያጠናቅቁ ጀርመን ደግሞ 4ኛ ደረጃ በመያዝ ማጠናቀቃቸውን ከዓለም አትሌቲከስ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። 

በሴቶች የዓለም የግማሽ ማራቶን ሻምፒዮና ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው በሴቶች 1፡05፡19 በሆነ ሰዓት 3ኛ ደረጃ በመያዝ ውድድሩን አጠናቅቃለች። 

ኬኒያዊቷ ጄፕችርችር ውድድሩን 1፡05፡16 ሰዓት በመግባት ክብረወሰን ጭምር በመስበር በአንደኝነት ስታጠናቅቅ ለጀርመን የምትሮጠው ሜላት ይስሃቅ ኬጄታ ደግሞ 1፡05፡18 በሆነ ሰዓት ሁለተኛ ደረጃን ይዛ ጨርሳለች።

ውድድሩን አትሌት ዘይነባ ይመር እና አባበል የሻነህ 4ኛ እና 5ኛ ሆነው ሲያጠናቅቁ አትሌት ነፃነት ጉደታ 8ኛ ሆና ጨርሳለች።

በወንዶች የግማሽ ማራቶን ሻምፒዮና ኢትዮጵያው አትሌት አምደወርቅ ዋለልኝ 59 ደቂቃ 08 ሴኮንድ በሆነ ሰዓት በመግባት 3ኛ ደረጃ ይዞ ውድድሩን አጠናቅቋል።

ውድድሩን ኡጋንዳዊው ጃኮብ ኪፕሊሞ በ58 ደቂቃ 49 ሴኮንድ በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ ኬኒያዊው ካንዴ ደግሞ 58 ደቂቃ 54 ሴኮንድ በሆነ ሰዓት 2ኛ ደረጃን በመያዝ ጨርሷል። 

ሌሎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች (አንዱአምላክ በልሁ፣ ልኡል ገ/ስላሴ እና ኃይለማርያም ኪሮስ) በቅደም ተከተል 5ኛ፣ 10ኛ እና ሆነው አጠናቅቀዋል

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish