Home Sport News የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ

የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ

by sam

የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የ2020/21 የምድብ ጨዋታዎች ከምድብ 5-8 ዛሬ ምሽት በተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

ከነዚህ ውስጥ በምድብ 8 ፒኤስጂ ማንችስተር ዩናይትድን ምሽት 4 ሰዓት ላይ የሚያስተናግድበት ጨዋታ ከፍተኛ ትኩረት አግኝቷል፡፡

በምሽቱ ጨዋታ በዩናይትድ በኩል አንበሉ ሃሪ ማጉየር፣ ኤሪክ ቤይሊ፣ ኤዲሰን ካቫኒ እና ማውሰን ግሪንውድ ወደ ፓሪስ ባቀናው ቡድን ውስጥ አልተካተቱም፡፡

በዚሁ ምድብ የሚገኙት አር ቢ ሌፕዚግ እና የኢስታንቡሉ ባሻክሼርም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

በሌሎች ጨዋታዎች ቼልሲ ከሲቪያ፣ ሬንስ ከክራንስኖዳር፣ ዜኒት ሴንት ፒተርስበርግ ከክለብ ብሩጅ፣ ላዚዮ ከቦርሲያ ዶርትመንድ፣ ዳይናሞ ኪየቭ ከጁቬንቱስ፣ ባርሴሎና ከፌረንቫሮስ  እንደሚገናኙ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish