Home Sport News የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በሴካፋ ውድድር ለመሳተፍ ወደ ርዋንዳ አቅንቷል

የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በሴካፋ ውድድር ለመሳተፍ ወደ ርዋንዳ አቅንቷል

by sam

ኢትዮጵያን ጨምሮ 7 ሀገራት የሚሳተፉበት ከ17 ዓመት በታች የሴካፋ የምስራቅና መካከለኛ አፍሪካ ዋንጫ ውድድር ከፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ በርዋንዳ አስተናጋጅነት ይካሄዳል።

20 ተጫዋቾችን ያካተተው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በሻምፒዮናው ለመሳተፍ ዛሬ ጠዋት ወደ ስፍራው አቅንቷል።

ብሔራዊ ቡድኑ በምድብ አንድ ከኡጋንዳ ኬንያና ደቡብ ሱዳን ጋር የተደለደለ ሲሆን በምድብ ሁለት አስተናጋጇ ርዋንዳ ጅቡቲና ታንዛኒያ ይገኙበታል።

ውድድሩ ከፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ ለ10 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ብሄራዊ ቡድኖች የወደፊት ተተኪ እግር ኳስ ተጫዋቾችን አቅም የሚፈትሹበት ታዳጊዎችም ብቃታቸውን ለማሳየት እድል የሚያገኙበት ነው።

በሻምፒዮናው የመካከለኛና ምስራቅ አፍሪካን በ2021 በሞሮኮ አስናጋጅነት በሚካሄደው አህጉራዊ ከ17 ዓመት በታች እግር ኳስ ዋንጫ ቀጠናውን የሚወክሉ ብሔራዊ ቡድኖች የሚመረጡ ይሆናል።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish