Home Sport News የዘንድሮ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ተሳታፊዎች ቁጥር ወደ 12 ሺህ 500 ዝቅ መደረጉ ተገለፀ

የዘንድሮ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ተሳታፊዎች ቁጥር ወደ 12 ሺህ 500 ዝቅ መደረጉ ተገለፀ

by sam

ነገ ምዝገባ በሚጀምረው 20ኛው ቶታል ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 12 ሺህ 500 ተሳታፊዎች እንደሚካሄድ ተገለፀ።

የኮቪድ-19 ቅድመ ጥንቃቄዎችን ተቀዳሚ በማድረግ ጥር 2 2013 ዓ.ም የሚካሄደው 20ኛው ቶታል ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ምዝገባ በነገው እለት እንደሚጀመርም ተገልጿል።

የውድድሩ ምዝገባ ከታህሳስ 2 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ተሳታፊዎች በያሉበት አሞሌን በመጠቀም እንዲያካሂዱ ዝግጅቱ መጠናቀቁን የገለጸው ታላቁ ሩጫ፤ የመመዝገቢያ ዋጋውም 450ብር መሆኑን ገልጻል።

የዚህ ዓመት ታላቁ ሩጫ የውድድር መነሻ መስቀል አደባባይ ሲሆን መድረሻው ደግሞ አትላስ አካባቢ መሆኑንም ታላቁ ጫ በኢትዮጵያ በሰጠው መግለጫው አስታውቋል። 

በተጨማሪም የዓለም አቀፍ ተሳታፊዎችን ለማካተት ውድድሩ በሚካሄድበት ተመሳሳይ ቀን በቨርቹዋል ውድድር በያሉበት ተሳታፊ እንዲሆኑና የ20ኛውን ዓመት ክብረ በዓል አብረው እንዲያከብሩ ቅድመ ሁኔታ መጠናቀቁንም ገልጿል።

የጤና ሚኒስቴር ባወጣው መመሪያ መሰረት ከቀድሞ ተሳታፊ 25 በመቶ ብቻ አሳታፊ የሚደርገው ታላቁ ሩጫ  የኮቪድ-19 ቅድመ ጥንቃቄዎች ተግባራዊ እንብደሚያደርግም ተገልጿል።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish