Home Sport News የአውሮፓ ሊጎች አጫጭር መረጃዎች !

የአውሮፓ ሊጎች አጫጭር መረጃዎች !

by sam

• ሼፍልድ ዩናይትድ ያልተጠበቀ ሶስት ነጠብ ከ ኦልድ ትራፎርድ ይዘው ሲመለሱ አሸናፊ የሆኑበትን ግብ በ ኪን ብራየን እና ኦሊቨር ቡርክ አማካኝነት አግኝተዋል ።

• የ ዩናይትድን ብቸኛ ግብ ሀሪ ማጓየር ከመረብ ማሳረፍ ቢችልም ከሽንፈት ሊታደጋቸው አልቻለም ።

• ቶማስ ቱሄል እና ቼልሲ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ከ ዎልቭስ ጋር ሲያደርጉ በአቻ ውጤት ጀምረዋል ።

• ሼፍልድ ዩናይትድ በሊጉ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በኦልድ ትራ ፎርድ ድል ማድረግ ችለዋል ።

• የምሽቱን ድል ተከትሎ ሼፍልድ የ ዩናይትድ የ አስራ ሶስት ጨዋታ ያለመሸነፍ ጉዞ ረተዋል ።

• ጁቬንቱስ በ ፍራቦታ ፣ ኬዛ ፣ ሞራታ እና ኩሉሴቪስኪ ጎሎች ስፓልን በማሸነፍ በኮፓ ኢታሊያ ቀጣዩን ዙር ተቀላቅለዋል ።

• ጁቬንቱስ በቀጣይ ዙር ከ ኢንተር ሚላን ጋር የሚጫወቱ ይሆናል ።

• የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና በ ሜሲ እና ዲዮንግ ግቦች ራዮ ቫይካኖን 2 ለ 1 በማሸነፍ በ ኮፓ ዴ ላሬ ቀጣዩን ዙር መቀላለቀላቸውን አረጋግጠዋል ።

• ሊዮኔል ሜሲ በ ኮፓ ዴ ላሬ ያስቆጠራቸውን የግብ መጠን ወደ 54 ከፍ ማድረግ ችሏል ።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish