Home Sport News ቼልሲ እና ሙኒክ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፉ !

ቼልሲ እና ሙኒክ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፉ !

by sam

• የለንደኑ ክለብ ቼልሲ በአስደናቂ ብቃታቸው ሲቀጥሉ የላሊጋውን መሪ አትሌቲኮ ማድሪድ በኤመርሰን እና ዚያች ጎል አሸንፈዋል ።

• ሙኒክ በተመሳሳይ ሁኔታ ላዚዮን በ ሊዋንዶውስኪ እና ሞቲንግ ጎሎች በማሸነፍ በቀላሉ ቀጣዩን ዙር ተቀላቅለዋል ።

• አትሌቲኮ ማድሪድ ባለፉት አስር ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻሉት በሶስቱ ብቻ ነው ።

• ንጎሎ ካንቴ እና ጆሽዋ ኪሚክ የምሽቱ ጨዋታ ኮከብ በመባል ተመርጠዋል ።

• የቼልሲው ግብ ጠባቂ ሜንዲ በሻምፒየንስ ሊጉ ከተሞከሩበት ሀያ ሙከራዎች አስራ ዘጠኙን ማዳን ችሏል ።

• ሜንዲ ከዚህ በተጨማሪም በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ካደረጋቸው ሰባት ጨዋታዎች በስድስቱ መረቡን አላስደፈረም ።

• ባየር ሙኒክ ወደ ሩብ ፍፃሜው ለአስራ ዘጠነኛ ጊዜ ማለፋቸውን ተከትሎ በውድድሩ ታሪክ የመጀመሪያው ቀዳሚ ክለብ ሆነዋል ።

• ቼልሲዎች ቶማስ ቱሄል ቡድኑን ከተረከቡ በኋላ ባደረጓቸው አስራ ሶስት ጨዋታዎች ባለ መሸነፍ ቀጥለዋል ።

• ሪያል ማድሪድ ብቸኛው የላሊጋው ተወካይ በመሆን በሩብ ፍፃሜው የሚሳተፍ ይሆናል ።

• የቼልሲው ኤመርሰን ያስቆጠራት ግብ በሻምፒየንስ ሊጉ ታሪክ የተቆጠረችው 9,000ኛ ጎል ሆናለች ።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish